የፓራሜድ ኮሌጁ ጥናትና ምርምር እና የማኅበረሰብ አገልግሎት ክፍል የተለያዩ ጥናቶች በማከናወን ጥናቶቹን ወደ ተግባር በማውረድ ለማህበረሰቡ ጥቅም የሚሰጡ ከፍተኛ ሥራዎች እያከናወነ ይገኛል፡፡ በቀን 01/09/2016 ዓ.ም. ከአ/ም/መንግስት ት/ቤት ለተውጣጡ 32 ተማሪዎች ስነ-ተዋልዶ ጤና እና ኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከያ ላይ ያተኮረ ስልጠና የተሰጠ እና በቀጣይ ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በሚሄዱበት ወቅት ሊያጋጥሟቸው የሚችሉ ተግዳሮቶችን እንዴት መቋቋም እንዳለባቸው የትኩረት ስልጠና ነው የተሰጠው። ስልጠናውን ከወሰዱት መካከል 17ቱ ሴቶች ሲሆኑ ሁሉም ሰልጣኝ ተማሪዎች በተሰጣቸው ስልጠና እጅግ ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸው ከስልጠናው ያገኟቸውን ትምህርቶች ራሳቸውንም ሆነ ጓደኞቻቸውን ለመጠበቅ በተግባር ላይ እንደሚያውሉ አረጋግጠዋል::

የኮሌጁ የጥናትና ምርምር እና የማሕበረሰብ አገልግሎት ክፍል ኃላፊ እንደገለጹ ከሆነ ኮሌጁ በቀጣይ ወደ ተለያዩ ወረዳዎች በማቅናት ስልጠናዎችን ለመስጠት እንዳቀደ እና በትምህርት ቤቶችና በሌሎች ባለድርሻ አካላት አስፈላጊው ትብብር እንዲደረግላቸው ጠይቀው፣ ኮሌጁ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች መጠነ ሰፊ የሥልጠና ጥቅሎችን ያዘጋጀ ስለሆነ አብሮ መስራት ለሚፈልጉ ሁሉ በሩን ክፍት አድርጎ እንምጠብቅ አክለው ገልፀዋል!!