በ2015 ዓ.ም. የ12ኛ ክፍል ፈተና ወስደው ውጤታቸው ከ50 በታች በመሆኑ ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግባት ያልቻሉ ነገር ግን በአንፃራዊነት የተሻለ ውጤት የነበራቸው ተማሪዎች በመንግስትና በግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ የአንድ ሴሚስተር ማካካሻ ትምህርት ወስደው በተቋማትና በማዕከል የሚሰጠውን ምዘና በሚያስመዘግቡት ውጤት መሠረት ከ2016 ዓ.ም. ፍሬሽማን ተማሪዎች ጋር የከፍተኛ ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ በትምህርት ሚኒስቴር የተቀመጠውን አቅጣጫ ተከትሎ ወደ 300 የሚጠጉ ተማሪዎችን ተቀብሎ እውቅ መምህራንን መድቦና ለዚህ መርሐ-ግብር ብቻ አስፈላጊውን ማቴሪያል ገዝቶ በማቅረብ ተማሪዎችን አሰልጥኖ በማብቃት ከመስከረም 7 – 10/ 2016 ዓ.ም. የማካካሻ (Remedial) ፈተና እንዲወስዱና ወደ ዩኒቨርሲቲ ፍሬሽማን አድርጓል፡፡