ፖራሜድ ኮሌጅ 30 የሚሆኑ ወንበሮችን ለአርባምንጭ ሆስፒታል አበረከተ!!

ፖራሜድ ኮሌጅ ከአርባምንጭ ሆስፒታል በቀረበለት ጥያቄ መሠረት በኮሌጁ የጥናትን ምርምርና የማሕበረሰብ አገገልግሎት ክፍል በኩል 30 የሚሆኑ ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ ወንበሮችን አበርክቷል። የኮሌጁ አመራሮች እንደገለጹት ኮሌጁ የሆስፒታሉን የህክምና ቁሳቁሶች በማሟላት ረገድ ከዚህ ቀደምም ጉልህ ሚና ሲጫወት ቆይቷል። ከዚህም በኋላ እንደ አንድ የሆስፒታሉ ባለድርሻ አካል ድጋፉ የየሚቀጥል መሆኑ ተገልጿል።በሆስፒታሉ በኩል የተገኙ አመራሮችም ፓራሜድ ኮሌጅ የሁልጊዜ አጋር በመሆን ላበረከታቸው አስተዋፅኦዎች ምስጋናቸውን የገለጹ ሲሆን ትብብሩ በተለያዩ መስኮች እንዲቀጥልና ሌሎችም ተቋማት የፓራሜድ ኮሌጅን ፈለግ እንዲከተሉ አሳስበዋል!!