ፓራሜድ ኮሌጅ በአ/ም/ከተማ አስተዳደር በማህበረሰብ አገልግሎት ላበረከተው አስተዋጽኦ ዕውቅና ተሰጠው!!

ኮሌጁ በርባምንጭ ከተማ አስተዳደር ስር ለሚገኙ ከ 50 በላይ አቅመ ደካማ ቤተሰቦች የጤና መድህን ሽፋን በማድረጉ ከከተማ አስተዳደሩና የኢትዮጵያ የጤና መድኅን አገልግሎት ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የዕውቅና የምስክር ወረቀት ተሰጥቶል፡፡ ኮሌጁ በተለያዩ ማህበረሰብ አቀፍ አገልገሎቶች ላይ በመሳተፍ ሕብረተሰቡን በመደገፍ ከሚታወቁ ተቋማት መካከል ግንባር ቀደም ሲሆን በቀጣይም የኮሌጁን ድጋፍ በሚሹ አገልግሎቶች ላይ በመሳተፍ የድርሻውን አስተዋጽኦ ለማበርከት ይተጋል፡፡