ፓራሜድ ኮሌጅ ለድልፋና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የጤና ቡድን የስፖርት ትጥቆች አበረከተ!!

ኮሌጁ በጥናትና ምርምር እንዲሁም የማህበረሰብ አገልግሎት ክፍል በኩል በድልፋና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የጤና ቡድን አባላት በኩል በተደረገለት ጥሪ መሰረት የኮሌጁ ስራ ኃላፊዎችና የሆስፒታሉ አመራሮች እንዲሁም የጤና ቡድኑ አባላት በተገኙበት ለ41 የቡድኑ አባላት የሚሆን መለያና ቁምጣ ግዥ በመፈጸም አስረክቧል፡፡ በርክክቡ ወቅት የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ ዶ/ር ወንድሙ ጫርፌ ኮሌጁ ላደረገላቸው ፈጣን ትብብርና ድጋፍ ምስጋናቸውን በማቅረብ ከኮሌጁ ጋር በጋራ ለመስራት እንዲሁም ድጋፍ ለማድረግ የሁለጊዜም ዝግጁነታቸውን አረጋግጠዋል፡፡ ኮሌጁን በመወከል የተገኙት የኮሌጁ ስራ አስኪያጅ እና ባለቤት በበኩላቸው የጤና ተቋማት ከድልፋና ሆስፒታል አርኣነት ያለው ተግባር ብዙ ትምህርት መቅሰም እንደሚገባቸው ጠቅሰው በጤናው መስክ እንደተሰማራ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም የጤና አገልገሎት ሰጪ ተቋማት ባለድርሻ አካላት በመሆናቸው የተጀመረው ድጋፍ በልዩ ልዩ ዘርፍ እንደሚቀጥል አሳስበዋል፡፡ በመርሃ ግብሩ የተገኙት የቡድን አባላትም ምስጋናቸውን ያቀረቡ ሲሆን ኮሌጁን በማስተዋወቅ በኩል የድርሻቸውን ለመወጣት ቃል በመግባት የመርሃ ግብሩ ፍጻሜ ሆኗል፡፡