በ15/03/2017 ዓ.ም. ከፌዴራል ስራና ክህሎት ሚኒስትር፣ ሚኒስቴር ደኤታ በዶ/ር ተሻለ በረቻ የተመራ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ቡድን በፓራሜድ ኮሌጅ ቴ/ሙ/ ት/ስልጠና መርሐ- ግብር አስመልክቶ የመንግስት የስራ ጉብኝት አድርገዋል።
በጉብኝቱ ወቅት የፓራሜድ ኮሌጅ አደረጃጀትና ለቴ/ሙ/ት/ስልጠና የተቀመጠውን የትኩረት አቅጣጫ የተመለከቱ ሲሆን በዚህም የትምህርቶችን ሠርቶ ማሳያዎችን፣ ድጂታል ቤተ-መጻሕፍት፣ ኦን ላይን ፈተና (online exam) አሰጣጥን፣ የእንስሳት ጤናና የእንስሳት እርባታ ላቦራቶሪ ቁሳቁሶችን (laboratory materials) ከመመልከታቸው ባሻገር አዲሱን የተማሪዎች ምዘናና ውጤት አመዘጋገብ (Grade reporting system) ተመልክተው በማድነቅ ገንቢ አስተያየት ሰጥተዋል፡፡
በጉብኝቱ ወቅት በተደረገው ውይይት ከተነሱትን ዋና ዋና ነጥቦች መካከል፡ በክልላችን የሚገኙ ወጣቶች የቴ/ሙ/ ት/ስልጠና ወስደው እውቀታቸውንና ክህሎታቸውን በማዳበር በአገርቱ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ንቁ ተሳታፊ ሆነው ሕይወታቸውን በአግባቡ እንዲመሩ የሚያደርጋቸውን መርህ በመከተል ስራ ጠባቂ ሳይሆን ስራ ፈጣሪ የሆነውን ትውልድ ማፍራት እንዳለብን ተመላክቷል፡፡
በአጠቃላይ በፓራሜድ ኮሌጅ የተመለከቱት ሁሉ ተስፋ ሰጭ መሆኑን በማረጋገጥ ኮሌጁ ከስልጠናው ጋር ተያይዞ በሚያከናውናቸው ስራዎች ከመንግስት በኩል አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚደረግ አረጋግጠዋል፡፡
.



Recent Comments